አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ (Ante Gen Yaw Ante Neh) - በረከት ፡ ፈቃዱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
በረከት ፡ ፈቃዱ
(Bereket Fekadu)

Bereket Fekadu 2.jpg


(2)

ሞት ፡ መሻገሪያዬ
(Mot Meshageriyayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ፈቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Fekadu)

እስከዛሬ እኔ ያየሁት ሃ የተረዳሁት
መልካምነትህን ነዉ የማዉቀው አታውቅም ክፋት
ባለፍኩበት ሁሉ ከኔ ጋር የሆንክ
የልጅነቴ አምላክ እግዚአብሔር
አይኔ ያየው ይሄንን ነው መልካምነትህን ነው
አይኔ ያየው ይሄንን ነው መልካምነትህን

አሃ መንገዴን ሁሉ እየመራኸኝ
ያልተለወጥክብኝ አንተ ብቻ ነህ
አንተ ግን አንተ ነህ አንተ ብቻ ነህ

ሁሉ ፡ ሲለዋወጥ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኣትለዋወጥም
ነገር ፡ ሲለዋወጥ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አትለዋወጥም

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ነህ (፪x)

አንዴ ፡ ስንወድቅ ፡ አንዴ ፡ ስንነሳ ፡
ያሳለፍነው ፡ ነገር ፡ እስኪ ፡ እንዴት ፡ ይወሳ
በጠራነው ፡ ጊዜ ፡ ለአፍታም ፡ ሳይዘገይ ፡
እዚ ፡ ያደረሰን ፡ እሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ እሱ እንዴት ድንቅ ነው(፪x)

ሁሉ ፡ ሲለዋወጥ ፡ አሃ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ነህ ፡ አትለዋወጥም
ነገር ፡ ሲለዋወጥ ፡ አሃ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አትለዋወጥም

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ነህ (፪x)

ጭንቅ ጥብብ ብሎን ፡ ማን ፡ አለልኝ ፡ ስንል
በኛ ፡ ላይ ፡ ምክሩ ፡ በርትቶ ፡ ሲያይል
የተረሳን ፡ መስሎን ፡ ከመከራው ፡ ብዛት ፡
ግን ፡ እሱ ፡ አቆመን ፡ እየሆነ ፡ አባት

በማደርያው: ላይ ፡ ያለኸው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለኸው ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ነህ (፪x)

ሁሉ ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣሃ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ አትለዋወጥም
ነገር ፡ ሲለዋወጥ ፡ ኣሃ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ አትለዋወጥም

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ እርሱ ፡ እንዴት ድንቅ ነው (፪x)

ከርሱ ፡ ጋር ፡ ስንጎዝ ፡ ባለፉት ፡ ዘመናት ፡
ስንቴ ፡ አሳለፈን ፡ ክፉዎቹን ፡ ቀናት
እጃችንን ፡ ይዞ ፡ በድል ፡ እየመራ ፡
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ በምረቱ ፡ ኣቆመን

በማደርያው ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ያዉ ፡ እርሱ ፡ ድንቅ ነው (፬x)