ዓለም ፡ በቃኝ (Alem Beqagn) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ከኢየሱሴ ፡ በላይ
በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
ሌላው ፡ ነገር ፡ አያስደንቀኝም ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ

በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ
በቃ ፡ ተቀበለኝ ፡ በቃኝ
በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ
በቃ ፡ ዓለም ፡ በቃኝ (፪x)

በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ
ሊቀ ፡ ካህን ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ
በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ
የመረጠኝ ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ

አልተሳሳትኩም (፪x) ፡ በምርጫዬ
ቀን ፡ ቆጠረና ፡ ዋጋ ፡ ከፈለኝ ፡ በተራዬ (፪x)

ፍፁም ፡ ነው (፪x) ፡ ለእኔ ፡ የታየልኝ ፡ በጐ ፡ ስጦታው
ልቤን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ከአብ ፡ ያገኘሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው
መጽሐፉ ፡ ነግሮኛል ፡ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ ተቀምጠሃል ፡ ብሎ
ከዚህ ፡ የበለጠ ፡ ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ዘንድሮ

በዚህ ፡ ዓለም ፡ ካለው (፪x) ፡ ትልቅ ፡ ነኝ ፡ ካለው
በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል ፡ የተገለጠው (፪x)

በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ከኢየሱሴ ፡ በላይ
በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
ሌላው ፡ ነገር ፡ አያስደንቀኝም ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ

በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ
በቃ ፡ ተቀበለኝ ፡ በቃኝ
በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ
በቃ ፡ ዓለም ፡ በቃኝ (፪x)

በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ
ሊቀ ፡ ካህን ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ
በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ
የመረጠኝ ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ

ክብርህን ፡ ያየሁ ፡ ዕለት ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል
ሞገስህን ፡ ሳየው ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል
ግርማህንም ፡ ሳየው ፡ ልቤ ፡ ደስ ፡ ይለዋል
ፍቅርህን ፡ ሳየው ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል

ባለ ፡ ግርማ ፡ ነህ (፪x) ፡ ባለ ፡ ግርማ
ባለ ፡ ሞገስ ፡ ነህ (፪x) ፡ ባለ ፡ ሞገስ (፬x)