Awtaru Kebede/Lelitu Nega/Lebie Awqotal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
ዝም ፡ ብሎ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ ባይነጋ
ልማድ ፡ ሆኖብኛል ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ እስኪነጋ
ልማዴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር
አይችልም ፡ አትበሉኝ ፡ አይችልም ፡ አትበሉኝ
ሳይችል ፡ ይሄን ፡ ጌታ ፡ አይታቹሃል ፡ ወይ
ምስኪኑን ፡ አንስቶት ፡ ቀብቶት ፡ አታዩኝም ፡ ወይ
በተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ወስጥ ፡ በተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ወስጥ
በሩ ፡ ሳይከፈት ፡ ማንስ ፡ እስቲ ፡ ይገባል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለእርሱ ፡ ቀላል ፡ ሆኖ ፡ ሙሉ ፡ አይኔ ፡ አይቶታል
ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
ዝም ፡ ብሎ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
ስለሆነም ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ ስለተሳካ
በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ
ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ< (፪x)
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ ባይነጋ
ልማድ ፡ ሆኖብኛል ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር
ልቤ ፡ አውቆታል ፡ ለካ (፪x)
መዘመር ፡ አልተውም ፡ ሌሊቱ ፡ እስኪነጋ
ልማዴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ወጉን ፡ መናገር
እኔ ፡ እየዘመርኩ ፡ ተከፈተ ፡ ያ ፡ በር
ተው ፡ አይችለም ፡ አትበል
ተው ፡ ጌታ ፡ ይችላል ፡ እኮ (፪x)
ተይ ፡ አይችለም ፡ አትበይ
ተይ ፡ ጌታ ፡ ይችላል ፡ እኮ (፪x)
ውልቅ ፡ አድርጌ ፡ አወጣሁት ፡ አልመች ፡ ሲለኝ
እኔ ፡ የለመድኩት ፡ ተዓምር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ያሳይኝ
አልገዛልህም ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ለሌላው
አንበሳና ፡ ድብ ፡ መግደል ፡ ነው ፡ እኮ ፡ የእኔ ፡ ስራ (፪x)
ሰይፌ ፡ አይገባም ፡ ወደ ፡ ሰገባው
ህዝቡን ፡ ያሸበረው ፡ እስቲ ፡ የቱ ፡ ነዉ
የማይወድቅ ፡ ይመስላል ፡ ፊቴ ፡ ተገትሮ
አንዲት ፡ ቃል ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ያሳየኛል ፡ ጥሎ(፪x)