ረድኤቴ ፡ እግዚአብሔር (Redietie Egziabhier) - አስቴር ፡ ሞገስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስቴር ፡ ሞገስ
(Aster Moges)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ አልወርድም
(Enie Alwerdem)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Moges)

ረድኤቴ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አለህ ፡ ጉዳይ
የጀመርከውን ፡ ሳትጨርሰዉ
አታርፍምና ፡ ሳትፈጽመዉ (፪x)

ልቤን ፡ አሰፋህ ፡ ውስጤን ፡ አሰፋህ
ዙሪያዬን ፡ አሰፋህ ፡ አንተ ፡ ስትመጣ (፪x)

እጀህ ፡ ተዘርግቷል ፡ ማን ፡ ሊመልሰው
በረከትን ፡ ከላይ ፡ ሊያዠቅዢቀው (፬x)

ብቻህን ፡ ክበር ፡ አንተው ፡ ንጉሥ
የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ በክብር ፡ ተመላለስ (፪x)

አንተ ፡ ማንንም ፡ ጌታ ፡ የማትረሳ
ሁሉም ፡ በጊዜው ፡ አንተ ፡ የምታነሳ
የተናገርከውን ፡ አታዘገየው
እጅ ፡ በእጅ ፡ ውዲያው ፡ ሳታወራርደው (፪x)

ፊትህ ፡ አበራ ፡ ሞገስህ ፡ አበራ
ክብርህ ፡ አበራ ፡ አንተን ፡ ስጣራ (፪x)

ድጆች ፡ ተከፈቱ ፡ ተነቀለ ፡ መዝጊያው
በቃ ፡ ተሰበረ ፡ የብረት ፡ መወርወሪያው (፬x)

ብቻህን ፡ ክበር ፡ አንተው ፡ ንጉሥ
የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ በኃይል/በክብር ፡ ተመላለስ (፪x)

ተመላለስ ፡ በኃይልህ
ተመላለስ ፡ በክብርህ (፬x)