ትልቅ ፡ የሆነውን (Teleq Yehonewen) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

Aster Abebe 1.jpg


(1)

ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ
(Keber Yebeqah Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ትልቅ ፡ የሆነውን ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድሜ
መቼ ፡ አንገቴን ፡ ደፋሁ ፡ መች ፡ ሄድኩ ፡ አቀርቅሬ
የተማመንኩበት ፡ ኩራቴ ፡ ሆኖኛል
ትላንቴ ፡ ይመስክር ፡ ሰልፌን ፡ አሸንፏል ፤ ሰልፌን ፡ አሸንፏል (፪x)

ከፍታውን ፡ ተመኝቶ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ ያለ
ላፍታ ፡ ማን ፡ ተመቸው ፡ ማን ፡ ተደላደለ
ወርዷል ፡ ወደ ፡ ቦታው ፡ እርሱ ፡ ወዳዘዘለት
ልክን ፡ ማወቅ ፡ እያለ ፡ ኋላ ፡ ከመዋረድ
በዕውቀቱ ፡ ልቀት ፡ ማንስ ፡ ገለጠው
እንኳንስ ፡ የእርሱን ፡ ጥግ ፡ ጫፉን ፡ ማን ፡ ነካው
ሁሉም ፡ ከታች ፡ ሆኖ ፡ ይመለከተዋል
የእጁ ፡ ስራ ፡ ሁሉ ፡ ሲያደንቀው ፡ ይኖራል

ከቶ ፡ አልደፍርም ፡ አንደኛ ፡ ልለው
ሁለተኛ ፡ ሆኖ ፡ ማን ፡ ተከተለው
ሁሌ ፡ ብቻውን ፡ ሚመለክ ፡ ትልቅ
ሚጨምር ፡ ክብር ፡ ከትላንቱ ፡ ይልቅ (፪x)

ደጋግሞ ፡ ቢፎክር ፡ ቢጨምር ፡ ቀረርቶ
ልኩን አግብቶታል ከሰማያት ፡ ወርዶ
ዝቅ ፡ ብሎ ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ታዞ ፡ በመስቀል ፡ ላይ
የአብን ፡ ጥም ፡ አርክቷል ፡ ሆኗል ፡ የአለም ፡ ሲሳይ
ግድግዳው ፡ ፈረሰ ፡ በመሀከል ፡ ያለው
ሰውን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ለይቶ ፡ ያቆየው
ፍቅር ፡ መሀል ፡ ገብቶ ፡ ሁሉን : አንድ ፡ አረገ
ጠላትም ፡ አፈረ ፡ ለሁሌ ፡ እጁን ፡ ሰጠ

ከቶ ፡ አልደፍርም ፡ አንደኛ ፡ ልለው
ሁለተኛ ፡ ሆኖ ፡ ማን ፡ ተከተለው
ሁሌ ፡ ብቻውን ፡ ሚመለክ ፡ ትልቅ
ሚጨምር ፡ ክብር ፡ ከትላንቱ ፡ ይልቅ (፪x)

ትልቅ ፡ የሆነውን ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድሜ
መቼ ፡ አንገቴን ፡ ደፋሁ ፡ መች ፡ ሄድኩ ፡ አቀርቅሬ
የተማመንኩበት ፡ ኩራቴ ፡ ሆኖኛል
ትላንቴ ፡ ይመስክር ፡ ሰልፌን ፡ አሸንፏል ፤ ሰልፌን ፡ አሸንፏል (፪x)