Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Hayal Aderekegn

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሥምህን ፡ አውቅኩት ፡ ተረዳሁት ፡ ደግሞም ፡ ታምኜበታለሁ
የፀና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ከስንቱ ፡ አምልጬ ፡ ተጠግቼው ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ
ደጅህን ፡ ጠናሁት ፡ አንኳኳሁት ፡ ከፍተህልኝ ፡ ተቀብለኸኛል
በፍቅር ፡ እጆችህ ፡ እቅፍ ፡ አርገህ ፡ ወደ ፡ ራስህ ፡ አስጠግተኸኛል (፪x)


አቤት ፡ ያለው ፡ ሰላም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጠጋጉ ፡ ወደ ፡ ደረትህ
ማዳመጥ ፡ ስትናገር ፡ የፍቅርን ፡ ቋንቋ
መቼ ፡ ይታወቃል ፡ ወፎቹ ፡ ሲንጫጬ ፡ ለሊቱም ፡ ሲነጋ (፪x)

ኃያል ፡ ሆይ ፡ በኃይልህ ፡ ኃያል ፡ አደረግከኝ
ብርቱ ፡ ሆይ ፡ በብርታትህ ፡ ብርቱውን ፡ አደረግከኝu
እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ
እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ (፪x)

በልዑሉ ፡ አምላክ ፡ መጠጊያ ፡ መኖሬ
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ማደሬ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ በላባዎቹ ፡ ጋርዶኝ
ከጠላት ፡ ፍላፃ ፡ አንዱም ፡ አላገኘኝ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

በአጠገቤ ፡ ሺህ ፡ በቀኜም ፡ አስር ፡ ሺህ
እየበተነልኝ ፡ ሆኛለሁ ፡ ድል ፡ ነሺ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል
አስጥሎኛል ፡ እንዲህ ፡ አድርጎ
ከአንደበቴ ፡ ምስጋናን ፡ ወዶ (፰x)

}}