Agegnehu Yideg/Chelemayie Bera/Lemen Eferalehu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን/እንዴት ፡ እፈራለሁ
አምና ፡ ንም ፡ ካቻ ፡ አምና ፡ ንም ፡ ሁሉን ፡ አይቻለሁ

አምናንም ካችአምናንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x)

ሸለቆ ተራራው ከፍታው ዝቅታው አቤት ከእርሱ ጋራ ከፊት ከፊት ሲሄድ እጄን ይዞ እኔን እየመራ አዎ አይቸዋለሁኝ ጥበቃውን ምህረቱን ለልጁ እንዳበዛ ዛሬም ቢሆን አምነዋለሁ አይተወኝም እንዲሁ እንደ ዋዛ

አዝ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምናንም ካችአምናንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x)

ከእናቱ ቤት ከአባቱ ከዘመዱ አብርሃምን ብቻውን ጠራና እኔ ወደ ማሳይህ አገር ሂድ ብሎ አዘዘውና አዎ ቃልኪዳን ገባለት ሊባርከው ለዘሩ ምድርን ሊያወርሰው እንደ ተናገርው የብዙ ህዝብ አባት አደረገው

አዝ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምናንም ካችአምንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x)

በቃሉ ተናግሮኝ ጠብቄው በፀሎቴ ምንም አልነሳኝም አባት አለኝ ብዬ ተመክቼ አላሳፈረኝም አዎ በፍፁም አልሰጋም ትደላደልኩ በአባቴ ቤት እግሬ ተተከለ ነገም ለሚሆነው አልፈራም አማኑኤል አለ

አዝ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምናንም ካቻአምናንም ክንዱን አይቻለሁ አምናንም ካቻ አምናንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x)