Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Yeiemahus Mengedegnoch

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የተስፋን ቃል የሰጣችሁ የታመነ ነውና በስፍራችሁ ሆናችሁ ጠብቁት ታገሱና እግዚአብሔር አይጨክንም ያስብላችኋል እርሱ ሰብሯችኋልና እርሱ ይጠግናችኋል

አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ

ጠውልጋችሁ ዝላችኋል የምትሉትን አታውቁም ስንፍናና ዝንጉነትን ለምን ከእናንተ አታርቁም እግዚአብሔር እረስቶናል እባካችሁን አትበሉ የሚበዣችሁ ኢየሱስ ታማኝ ነው እኮ ለቃሉ

አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ

ይቤዠናል ብለን ነበረ ተስፋ ያደረግነው ለካስ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደዚህ ዓይነት አምላክ ነው ስለምን እንደዚህ ትናገራላችሁ ጌታችን ከሞት ተነስቶ አሁን እኮ አለ አብሯችሁ

አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ

ኢየሩሳሌም ተመለሱ ስፍራችሁን ለቃችኋል እግዚአብሔር ያላችሁን በሙሉ ዘንግታችኋል የገባላችሁን ተስፋ እናንተ እንኳን ብትረሱ እግዚአብሔር ግን አይረሳም ከሞት ተነስቷል ንጉሡ

አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ