Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Nuro Kegieta Gar Temognal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

{{Lyrics | ርዕስ = ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ጥሞኛል | Title = Nuro Kegieta Gar Temognal | ዘማሪ = አዲሱ ፡ ወርቁ | Artist = Addisu Worku | Volume = 1 | አልበም = ክቡር ፡ ክቡር | Album = Kebur Kebur | Track = 10 | Year = | Lyrics = <poem> ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ጥሞኛል ከምለየው ፡ ሞት ፡ ይሻለኛል ይወደኛል ፡ እወደዋለሁ ሚስጢሬን ፡ አካፍለዋለሁ

ወዶኝ ፡ ቀርቧል ፡ ወደ ፡ ልቤ
ነፍሴን ፡ አጥግቧል ፡ ተርቤ
ሌላ ፡ ጌታ ፡ አያሻኝም
እንደእርሱ ፡ አይሆንልኝም
አዝ፦ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ የግሌ ፡ መከታ
ከመከራ ፡ ያወጣኛል ፡ እጁን ፡ ልኮ ፡ ያድነኛል
ስሙ ፡ ይክበር (፪x)

ወንድም ፡ ጋሻዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ታማኝ ፡ ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በመከራ ፡ ያጸናኛል ፡ በደስታው ፡ ይሞላኛል

ልቤን ፡ በፍቅሩ ፡ ያከታል
ጠላቴን ፡ ይቀጠቅጣል
እስከሞቴ ፡ አልተወውም
ስሙን ፡ ጠርቼ ፡ አልጠግብም
አዝ፦ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ የግሌ ፡ መከታ
ከመከራ ፡ ያወጣኛል ፡ እጁን ፡ ልኮ ፡ ያድነኛል
ስሙ ፡ ይክበር (፪x)

ሳለቅስ ፡ እምባዬን ፡ ያብሳል ከወላጅ ፡ እናት ፡ ይብሳል ለዘለዓለም ፡ አይለይም ስሙን ፡ ጠርቼ ፡ አልጠግብም

የድሆች ፡ አባት ፡ እርሱ ፡ ነው
ጉስቁልናን ፡ የቀመሰው
መሪአችን ፡ ነው ፡ አለቃችን
እናክብረው ፡ አባታችን

አዝ ስሙ ይክበር የእኔ ጌታ የእኔ የግሌ መከታ ከመከራ ያወጣኛል እጁን ልኮ ያድነኛል ስሙ ይክበር (፪x)

ስሙ ይክበር (፫x)