ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (Gietayien Akebralehu) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 1.png


(1)

ክቡር ፡ ክቡር
(Kebur Kebur)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

 
አነባ ፡ ጌታዬ ፡ አፈር ፡ ላይ ፡ ተደፍቶ
የወደቀበትን ፡ ጭንቀት ፡ ተመልክቶ
ጌታዬ ፡ ተጨንቆ ፡ አባዬ ፡ ሆይ ፡ አለ
አጋዥ ፡ አልተገኘም ፡ ለጌታ ፡ የዋለ

መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ትከሻው ፡ ተላጠ
ግርፋቱ ፡ በዛ ፡ ገላዉ ፡ ተመለጠ
ራቁቱን ፡ ደም ፡ ሲያፈስ ፡ በቀራንዮ ፡ ዋለ
አንገቱ ፡ ደፋ ፡ ሲል ፡ ዕዳ ፡ ተከፈለ

አዝጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ

ዝናን ፡ ከበሬታን ፡ ሞገስን ፡ በሥጋ
ሊያገኝ ፡ ወዶ ፡ ነፍሱን ፡ ከዓለም ፡ ከሚያስጠጋ
ይሻላል ፡ ጭጋፉ ፡ ውዳቄን ፡ እኔን፡ መሳይ
በሥጋው ፡ ተንቆ ፡ በእምነት ፡ ጌታን ፡ የሚያይ

አዝጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ

ማቆ ፡ በመከራ ፡ ጐስቋላ ፡ አካል ፡ ይዞ
በረሃን ፡ የሚዘልቅ ፡ ጌታን ፡ ተመርኩዞ
ተሸማቆ ፡ ኑሮውን ፡ ለጌታ ፡ ሲል ፡ ችሎ
ያለፈን ፡ አየሁት ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ

አዝጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ

በሞቱ ፡ ሊመስለዉ ፡ ጌታን ፡ ተከትሎ
ወድቆም ፡ የሚነሳ ፡ አልሸነፍ ፡ ብሎ
ለጠላቱ ፡ ታግሎ ፡ የማታ ፡ የማታ
ጌታው ፡ ምሎለታል ፡ እርሱ ፡ እንደሚረታ

አዝጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ
ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ


Navigation menu