ማን ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር (Man Ende Egziabhier) - አዲሱ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዲሱ ፡ ወርቁ
(Addisu Worku)

Addisu Worku 2.jpeg


(2)

አንዴ ፡ ቆርጠናል
(Andie Qortenal)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲሱ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisu Worku)

ዘንዶውን ፡ የወጋህ ፡ እባቡን ፡ የረገጥክ
ባህሩን ፡ ሰንጥቀህ ፡ ህዝብህን ፡ ያሻገርክ
በክብር ፡ ያረገህ ፡ በክብር ፡ የምትመጣ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ ነፃ ፡ የምታወጣ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ

አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ
የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል
ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x)

የእነ ፡ ሲድራቅ ፡ አምላክ ፡ የዳንኤል ፡ ታዳጊ
ከእቶን ፡ የምታድን ፡ የአምበሳን ፡ አፍ ፡ ዘጊ
በዘመናት ፡ ሁል ፡ ከህዝብህ ፡ ጋር ፡ የቆምክ
በከሳሻቸው ፡ ፊት ፡ ልጆችህን ፡ ያስከበርክ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ

አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ
የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል
ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x)

ሃያላን ፡ በግርማ ፡ ፈጥነው ፡ ሲሟሽሹ
በአክብሮት ፡ በፍርሃት ፡ ከፊቱ ፡ ሲሸሹ
መራፉን ፡ ይዘጋል ፡ ፍጥረት ፡ በቀጠሮ
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ይኖራል ፡ ዘላለም ፡ ተከብሮ(፪)

አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ
የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል
ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x)

ይሄ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ ከመረጠን
በጸጋው ፡ ሸፍኖ ፡ ህዝቤን ፡ አጅብ ፡ ካለኝ
አንተ ፡ ብቻ ፡ አምላክ ፡ ሁንልን ፡ ብለናል
ታቦቶቻችንም ፡ በእግርህ ፡ ስር ፡ ጥለናል
ለአንተ ፡ ተማርከናል

አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ
የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል
ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x)

ጠላቴ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል
ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል(፫x)